በአጠገቡም ቆሞ የነበረው አሞናዊው ጦቢያ፣ “ለመሆኑ የሚገነቡት ምንድን ነው? በድንጋይ የሚሠሩት ቅጥር እኮ ቀበሮ እንኳ ብትወጣበት ሊፈርስ ይችላል” አለ።
ከዚያም ቤን ሃዳድ፣ “ለሚከተለኝ ሰው ሁሉ የሰማርያ ዐፈር አንዳንድ ዕፍኝ የሚዳረስ ሳይሆን ቢቀር፣ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ሲል ሌሎች መልክተኞችን ወደ አክዓብ ላከ።
እርሱም፣ “አመጣጣቸው ለሰላምም ይሁን ለጦርነት ከነሕይወታቸው ይዛችሁ አምጧቸው” አለ።
“ ‘አሁን ናና፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋራ ተደራደር፤ የሚጋልቧቸው ሰዎች ካሉህ፣ ሁለት ሺሕ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።
ሖሮናዊው ሰንባላጥና አሞናዊው ሹም ጦቢያ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እስራኤላውያን ደኅንነት የሚቈረቈር ሰው በመምጣቱ እጅግ ተበሳጩ።
ነገር ግን ሖሮናዊው ሰንባላጥ፣ አሞናዊው ሹም ጦቢያና ዐረባዊው ጌሳም ይህን ሲሰሙ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ እንዲሁም፣ “የምታደርጉት ይህ ምንድን ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ።
እስከዚያች ጊዜ ድረስ ለበሮቹ መዝጊያ ባልገጥምላቸውም እንኳ፣ ቅጥሩን መሥራቴንና የቀረ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረባዊው ጌሳምና የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣
ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣ የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።
አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማንኛውም የርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።