ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።
ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤
በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤
በኤልያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።