ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤
ዘጠነኛው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛው ለሴኬንያ፣
ዐሥራ አንደኛው ለኤሊያሴብ፣ ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣
ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።
በኤልያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።
እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረ ገዥ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።
ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር።
ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ የሖሮናዊው የሰንባላጥ አማች ነበረ፤ እኔም ከአጠገቤ አባረርሁት።
ቀድሞ የአምላካችን ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ሆኖ የተሾመው ካህኑ ኤልያሴብ ነበር፤ እርሱም ከጦቢያ ጋራ የጠበቀ ወዳጅነት ነበረው፤
ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስሁ፤ በዚያም ኤልያሴብ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦቢያ አንድ መኖሪያ ክፍል በመስጠት የፈጸመውን ክፉ ድርጊት ተረዳሁ።
ሊቀ ካህናቱ ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ለሥራ ተነሡ፤ የበጎች በር የተባለውንም እንደ ገና ሠሩ። ቀደሱት፤ መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ላይ አቆሙ። መቶ ግንብ እስከሚባለው ግንብና ሐናንኤል ግንብ ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ሠርተው ቀደሱት፤