በጥልቁ ጕድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።
በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤ በጨለማ ጕድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።
ስለዚህ ኤርምያስን ወስደው፣ በዘበኞች አደባባይ በነበረው በንጉሡ ልጅ በመልክያ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በገመድም ኤርምያስን ወደ ጕድጓዱ አወረዱት። ጕድጓዱም ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ዘልቆ ገባ።