ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።
እንዳታይ ጨለማ የሆነብህ፣ ጐርፍም ያጥለቀለቀህ ለዚህ ነው።
የሞት ገመድ ዐነቀኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ።
እኔ በደነገጥሁ ጊዜ፣ “ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ” አልሁ፤ አንተ ግን ወደ አንተ ስጮኽ፣ የልመናዬን ቃል ሰማህ።
ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ፤ ጥልቅ ውሃም አይዋጠኝ፤ ጕድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ።
ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ።
በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመትቶ፣ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
ስለዚህ፣ “ክብሬ፣ ከእግዚአብሔርም ተስፋ ያደረግሁት ሁሉ ሄዷል” አልሁ።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ዐጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እንዲህም ይላሉ፤ ‘ዐጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ የለንም፤ ተቈርጠናል።’
የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።