በስተ ሰሜንም በኩል ወደ ሐናቶን ይዞርና በይፍታሕኤል ሸለቆ ላይ ይቆማል።
ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ ወደ ኒዓ ይታጠፋል።
ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።
ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ቤትዳጎን ይመለስና ዛብሎንንና የይፍታሕኤልን ሸለቆ ይዞ፣ ካቡልን በስተግራ በመተው በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤል ያቀናል።