ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ ወደ ኒዓ ይታጠፋል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በጋትሔፌር ነቢይ፣ በአማቴ ልጅ በባሪያው በዮናስ አማካይነት እንደ ተናገረው፣ ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ እስከ ሙት ባሕር ድረስ የነበረውን የእስራኤልን ድንበር አስመለሰ።
ከሣሪድም ወደ ምሥራቅ በመታጠፍ፣ የፀሓይ መውጫ ወደ ሆነው አገር ወደ ኪስሎትታቦር በመዝለቅ እስከ ዳብራት ሄዶ ወደ ያፊዓ ያቀናል።
በስተ ሰሜንም በኩል ወደ ሐናቶን ይዞርና በይፍታሕኤል ሸለቆ ላይ ይቆማል።