ኀያልና ቍጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ፣ ምድሬን ወሯታልና፤ ጥርሱ እንደ አንበሳ ጥርስ፣ መንጋጋውም እንደ እንስት አንበሳ መንጋጋ ነው።
ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።
ድኾችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
ስለ ሕዝቤ ምድር፣ እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣ ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣ ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ።
እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”
በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፤ የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።
“በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣ እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።