እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።
ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤ ዕዘኑ፤ ዋይ በሉ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ፣ ከእኛ አልተመለሰምና።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤ “ወዮ ለዚያ ቀን!”
እናንተ ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤ እናንተ የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤ የዕርሻው መከር ጠፍቷልና።
ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።
በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ወንዶች ልጆችን በዝሙት ዐዳሪዎች ለወጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም፣ ሴቶች ልጆችን ሸጡ።
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ሐምራዊና ቀጭን በፍታ የለበሰ፣ በየቀኑም በተድላ ደስታ የሚኖር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ።
እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ።