እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣ የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።
የያዕቆብ መኰብለል ለላባ በሦስተኛው ቀን ተነገረው።
ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ሁሉ ጋራ በንጉሡ ቤት ቅጽር በር ተኛ እንጂ፣ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር።
አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ፣ “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የኩሲ ምክር ይሻላል” አሉ፤ እግዚአብሔር በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት ሲል መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጓልና።
የእግዚአብሔርም ሰው፣ “ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” ሲል ለእስራኤል ንጉሥ ላከበት።
አድማቸውን እንዳወቅንባቸውና እግዚአብሔርም ዕቅዳቸውን ከንቱ እንዳደረገባቸው ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣ ሁላችን ወደ ቅጥሩ፣ እያንዳንዳችንም ወደየሥራችን ተመለስን።
እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ዛቻቸውንም ለመቋቋም ቀንና ሌሊት የሚጠብቁ ዘቦችን መደብን።
ኀጢአትህ አፍህን ታስተምረዋለች፤ የተንኰለኞችንም አነጋገር መርጠህ ትይዛለህ።
ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤
የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣ ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።
እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።
የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።
የግብጻውያን ልብ ይሰለባል፤ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖታትንና የሙታንን መናፍስት፣ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ምክር ይጠይቃሉ።
ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።
የሐሰተኞችን ነቢያት ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ ሟርተኞችን አነሆልላለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ እገለባብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ከንቱ አደርጋለሁ።
ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነውና።
ስለ ኤዶም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቷልን? ምክር ከአስተዋዮች ርቋልን? ጥበባቸውስ ተሟጧልን?
“ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰት እያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?
“በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣ አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?” ይላል እግዚአብሔር።
ጴጥሮስም ሲረጋጋ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁድ ካሰቡብኝ ሁሉ እንዳወጣኝ አሁን ያለ ጥርጥር ዐወቅሁ” አለ።
ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፣ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።