የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።
ሰዎች ቢዋረዱና አንተ፣ ‘ከፍ አድርጋቸው’ ብትል፣ እርሱ ዝቅ ያሉትን ያድናል፤
ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ ከነገሥታት ጋራ በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
ድኾችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።
ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
“ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።
የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”
እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፤ ኋላ ትጠግባላችሁና፤ እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፤ ኋላ ትሥቃላችሁና፤
ዘላለማዊ አምላክ መኖሪያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤ ‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
ዝቅ ያለው ወንድም ከፍ በማለቱ ይመካ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።