የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል? ማንስ ሊለጕመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?
በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’
“ስለ ብርታቱና ስለ አካላቱ ውበት፣ ስለ እጅና እግሩ ከመናገር አልቈጠብም።
አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን፣ የአፉን ደጅ ማን ደፍሮ ይከፍታል?
በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ ማስተዋል እንደሌላቸው፣ እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
ፈረሶች እንዲታዘዙልን ልጓም በአፋቸው ውስጥ ስናስገባ፣ መላ ሰውነታቸውን መምራት እንችላለን።