“ስለ ብርታቱና ስለ አካላቱ ውበት፣ ስለ እጅና እግሩ ከመናገር አልቈጠብም።
እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው? ከሰማይ በታች ማንም የለም።
የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል? ማንስ ሊለጕመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?