“ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣ በር የዘጋበት ማን ነው?
ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ።
ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
ለነፋስ ኀይልን በሰጠ ጊዜ፣ የውሆችን መጠን በለካ ጊዜ፣
ድንበር ወሰንሁለት፤ መዝጊያና መወርወሪያውን አበጀሁለት።
ደመናውን ልብሱ፣ ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣
በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤ ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ።
የእግዚአብሔርን ሥራ በዚያ አዩ፤ ድንቅ አድራጎቱንም በጥልቁ ውስጥ ተመለከቱ።
የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።
ወደ ሰማይ የወጣ፣ የወረደስ ማነው? ነፋስን በእጁ ሰብስቦ የያዘ ማነው? ውሆችንስ በመጐናጸፊያው የጠቀለለ ማነው? የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማነው? ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? የምታውቅ ከሆነ እስኪ ንገረኝ!
ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ ውሆችም የርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣ የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣
ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው?
ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።