ውሆች እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤ የጥልቁ ገጽ እንደ በረዶ ይጋገራል።
የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።
በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል? የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?
“ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጕም፣ ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን?
ያለፈበትን መንገድ ብሩህ ያደርጋል፤ ቀላዩንም ሽበት ያወጣ ያስመስለዋል።