በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል? የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?
የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።
ውሆች እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤ የጥልቁ ገጽ እንደ በረዶ ይጋገራል።
“ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣ በር የዘጋበት ማን ነው?
በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤