በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?
እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል።
እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቅቃሉ።
ስለ ክፋታቸውም፣ በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤
ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።
ከሰማይ ሁሉ በታች ብርሃኑን ይለቅቃል፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ይልካል።
“ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዝዘህ ታውቃለህን? ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?
ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ቅርጿ ይወጣል፤ ቅርጿ እንደ ልብስ ቅርጽ ጐልቶ ይታያል።
ኃጥኣን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። ሃሌ ሉያ።
ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ቦታው ተመለሰ። ግብጻውያን ከውሃው ሸሹ፤ እግዚአብሔርም ግብጻውያንን በባሕሩ ውስጥ ጣላቸው።