“ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዝዘህ ታውቃለህን? ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?
እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን”፣ ጨለማውን “ሌሊት” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን።
“ለመሆኑ ከሰው ሁሉ ቀድመህ የተወለድህ አንተ ነህን? ወይስ ከኰረብቶች በፊት ተገኝተሃል?
በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አይፈልጉም።
‘እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ፤ ማለፍ ግን አትችልም፤ የዕቡይ ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ አልሁት።
በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?
ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣ አንተስ በርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!
“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በርግጥ የምታስተውል ከሆንህ ንገረኝ።
እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።
ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው።
ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
ከአምላካችንም ጥልቅ ምሕረት የተነሣ፣ የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤
እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።