ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤ በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።
ይሁን እንጂ እኔን በማገልገልና የሌሎችን አገሮች ነገሥታት በማገልገል መካከል ያለውን ልዩነት ያውቁ ዘንድ፣ ለርሱ ይገዛሉ።”
የእግዚአብሔር ማጽናናት፣ በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?
በጆሯቸው ይናገራል፤ በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤
ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዝዛቸዋል።
ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣ በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
ድኻውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።
“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።
ድኾችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።
ድኻው በጮኸ ጊዜ፣ ችግረኛውና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።