ሕይወታቸው በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል ነው፣ ገና በወጣትነታቸውም ይቀጫሉ።
ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት።
ጊዜው ሳይደርስ ይጠወልጋል፤ ቅርንጫፉም አይለመልምም።
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።
“ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤ በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን።