“ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣ ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ።
በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም።
ትክክለኛ ጥበብ ባለብዙ ፈርጅ ናትና፣ የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ! እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።
“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን? ወይስ ሁሉን ቻዩን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?
መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው! የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
እኔም የምለው ይኖረኛል፤ የማውቀውንም እገልጣለሁ።
ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።
“ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ ማለትህ፣ ትክክል ይመስልሃልን?
“ለአንተና ዐብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።
“እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።
“ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅሥ እርሱ መልስ ይስጥ!”
ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤ እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጕዳት የሄደ ማን ነው?
ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ።
“እናንተ ግን፣ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስማ፤ መንገዴ ቀና አይደለችምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?