እግሬን በግንድ አጣብቋል፤ እንቅስቃሴዬንም ሁሉ ይከታተላል።’
እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ።
በዚያ ጊዜ በርግጥ ርምጃዬን ትከታተላለህ፤ ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።
እርሱ መንገዴን አያይምን? ርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ፤ በዐንገቱም የብረት ማነቆ ገባ።
ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።
የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።
እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋራ አጣብቆ አሰራቸው።