እርሱ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤ እኔም ከዐፈርና ከዐመድ አልተሻልሁም።
ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ ጋራ ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤
ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።
ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”
ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣ በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።
ከረግረግ አውጣኝ፤ እሰጥም ዘንድ አትተወኝ፤ ከጥልቅ ውሃ፣ ከእነዚያ ከሚጠሉኝ ታደገኝ።
ስለዚህ ኤርምያስን ወስደው፣ በዘበኞች አደባባይ በነበረው በንጉሡ ልጅ በመልክያ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በገመድም ኤርምያስን ወደ ጕድጓዱ አወረዱት። ጕድጓዱም ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ዘልቆ ገባ።