አምላክ በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዷል፤ በልብሴም ክሳድ ዐንቆ ይዞኛል።
ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጕሩ በክፉ ቍስል መታው።
አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።
ከቂልነቴ የተነሣ፣ ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤
ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ።