“እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣ በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤
ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”
ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።
የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤ የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።
ሥሬ ወደ ውሃ ይዘረጋል፤ ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድራል፤
የእህል ነዶ ጐምርቶ በወቅቱ እንደሚሰበሰብ፣ ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።
ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”
አንቺ፣ ‘በሊባኖስ’ ውስጥ የምትኖሪ፣ መኖሪያሽን በዝግባ ዛፍ የሠራሽ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ መከራ በላይሽ ሲመጣ ጩኸትሽ እንዴት ይሆን!
አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።
እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
“በተጭበረበረ ትርፍ መኖሪያውን ለሚገነባ፣ ከጠላት እጅ ለማምለጥ፣ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!