የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤ የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።
“እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣ በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤
“ደግሞም ሰው ታምሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣ በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤
ብርቱው አንበሳ ዐደን በማጣት ይሞታል፤ የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
ድኻውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።
ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣ በቁመናችን በዋጡን ነበር፤
በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣ እግዚአብሔር ይባረክ።
እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።
ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ ፀሓይን እንደማያይ ጭንጋፍ ይሁኑ።
ድኾችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጕረሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር።