ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤ የሚያነሣውም የለም፤ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣ በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።”
እብሪተኞች ያለ ምክንያት በደል አድርሰውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእዛዞችህን አሰላስላለሁ።
ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።
ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።
እንደ ሥራችሁ መጠን እቀጣችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱሯም እሳት እለኵሳለሁ፤ በዙሪያዋ ያለውንም ሁሉ ይበላል።’ ”
“በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ የቤን ሃዳድንም ዐምባ ይበላል።”
ከአንቺ ለማእዘን የሚሆን ድንጋይ፣ ለመሠረትም የሚሆን ዐለት አይወሰድም፤ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ፤” ይላል እግዚአብሔር።
እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።
ነገር ግን ልቡ በትዕቢት በጸናና በእብሪት በተሞላ ጊዜ ከዙፋኑ ተወገደ፤ ክብሩም ተገፈፈ።
ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣ በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣ በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
የቤን ሃዳድ ምሽጎች እንዲበላ፣ በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መኻል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።
የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣ በይሁዳ ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
“ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ በገዛ ምድሯ ተጣለች፤ የሚያነሣትም የለም።”
በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።
ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣ በእሳት ትቃጠላለች።