ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ ፈጽሞም ይደመሰሳል።
መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”
በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።
እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፣ ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት፤ ቍጣው ፈጥኖ ይነድዳልና። እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
አሕዛብም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል። የእስራኤል ቤት አሕዛብን ርስት ያደርጓቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ምድር ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዟቸዋል፤ የማረኳቸውን ይማርኳቸዋል፤ የጨቈኗቸውንም ይገዟቸዋል።
“እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣ እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ የሚቋቋሙህ፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።
ማንም ጕዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጕዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።
የማይሰማኝን ሕዝብ ግን ፈጽሜ እነቅለዋለሁ፤ አጠፋዋለሁም” ይላል እግዚአብሔር።
ይህን በመመልከት ላይ ሳለህ፣ አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ወረደ፤ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች መታቸው፤ አደቀቃቸውም።
ወዲያውኑም ብረቱ፣ ሸክላው፣ ናሱ፣ ብሩና ወርቁ ተሰባበሩ፤ በበጋ ወራት በዐውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራረጋቸው፤ ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሞላ።
ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፤ ለዘላለምም ይይዙታል፤ አዎን፤ ለዘላለም ይይዙታል።’
ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ፣ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል፤ ይታዘዙታልም።’
ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።
በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ ደግሞ የሚወድቅበትን ማንኛውንም ሰው ይፈጨዋል።”
ነገር ግን እኔ በላያቸው እንዳልነግሥ የፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ዕረዷቸው።’ ”