ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።
አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ ዐጡ።
ወደሚኖሩባትም ከተማ፣ በቀና መንገድ መራቸው።
እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ እንደ ሆነው ሁሉ፣ ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣ እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።
በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር አውራ መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራውያን ወደ ግብጽ፣ ግብጻውያንም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብጻውያንና አሦራውያን በአንድነት ያመልካሉ።
እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤
ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤ የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።
እንዲህ ይባላል፤ “አብጁ፤ አብጁ፤ መንገድ አዘጋጁ! ከሕዝቤ መንገድ ዕንቅፋት አስወግዱ።”
ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤ አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ! ድንጋዩን አስወግዱ፤ ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።