የከበሮ ደስታ ጸጥ አለ፤ የጨፋሪዎች ጩኸት አበቃ፤ ደስ የሚያሠኘውም በገና እረጭ አለ።
ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታም አይሰማበት።
በገናዬ ለሐዘን፣ እንቢልታዬም ለልቅሶ ተቃኝቷል።
እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን።
ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና።
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፣ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋራ ወደዚያ ይወርዳሉ።
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’
የደስታንና የእልልታን ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን አስቀራለሁ።
የደስታና የተድላን ድምፅ፣ የሙሽራና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም መንገዶች አጠፋለሁ፤ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለችና።
ሽማግሌዎች ከከተማዪቱ በር ሄደዋል፤ ጕልማሶች ዝማሬያቸውን አቁመዋል።
ዘፈንሽን ጸጥ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም የበገናሽ ድምፅ አይሰማም።
በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣ በዔድን ነበርህ፤ እያንዳንዱ የከበረ ድንጋይ አስጊጦህ ነበር፤ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ አልማዝ፣ መረግድ፣ ኢያሰጲድ፣ ሰንፔር፣ በሉር፣ ቢረሌና የከበረ ዕንቍ። ልብስህም የሚያብረቀርቅ ዕንቍ ወርቅ ነበር፤ የተዘጋጁትም አንተ በተፈጠርህበት ዕለት ነበር።
የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣ የዓመት በዓላቷንና የወር መባቻዎቿን፣ ሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓላቷን ሁሉ አስቀራለሁ።
ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናችሁ፤ መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።
የበገና ደርዳሪዎችና የሙዚቀኞች ድምፅ፣ የዋሽንትና የመለከት ነፊዎች ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምፅም፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም።