አዲሱ የወይን ጠጅ ዐለቀ፤ የወይኑም ተክል ደረቀ፤ ደስተኞችም ሁሉ አቃሰቱ።
ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና።
የሐሴቦን ዕርሻ፣ የሴባማም የወይን ተክል ጠውልጓል፤ የአሕዛብ ገዦች፣ ኢያዜርን ዐልፈው፣ ምድረ በዳውን ዘልቀው፣ ሥሮቻቸውን እስከ ባሕር ሰድደው የነበሩትን የተመረጡ የወይን ተክሎችን ረጋግጠዋል።
የደስታና የተድላን ድምፅ፣ የሙሽራና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም መንገዶች አጠፋለሁ፤ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለችና።
እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ የሚኖሩበትንም ስፍራ ከምድረ በዳው እስከ ዴብላታ ድረስ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”