እናንተ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤
ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤ በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣ በሐዘን ያለቅሳሉ።
ከሰይፍ፣ ከተመዘዘ ሰይፍ፣ ከተደገነ ቀስት፣ ከተፋፋመ ጦርነት ሸሽተዋልና።
የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።
እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ፤ ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ! “ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤ በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”
የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል።
በጠረፍ አገር የሚኖሩ ሁሉ፣ በአንቺ ሁኔታ ተደናገጡ፤ ንጉሦቻቸው በፍርሀት ራዱ፤ ፊታቸውም ተለዋወጠ።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፤ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጕዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።