ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።
በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።
ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ ቀኑ ደርሷልና። እግዚአብሔር በቀፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ ተነሥቷል።
የሚያውቁህን አሕዛብ ሁሉ፣ ሁኔታህ አስደንግጧቸዋል፤ መጨረሻህ የሚያሳዝን ሆነ፤ ከእንግዲህ ህልውና የለህም።’ ”
“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ያለ ሥጋት ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብጽ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።