እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።
ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።
እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።
በግብጽም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።
ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ፣ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ፣ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።
ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤
ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም፤ በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።
እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።
የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።”
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀኝ እጅህ በግርማ ከበረ፤ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀኝ እጅህ ጠላትን አደቀቀ።
በምዕራብ በኩል፤ የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣
ሌዋውያኑን በእግዚአብሔር ፊት አቅርብ፤ ከዚያም እስራኤላውያን እጃቸውን ይጫኑባቸው።
በእስራኤል በተወለዱት ተባዕት በኵሮች ሁሉ ምትክም ሌዋውያኑን ወስጃለሁ።
አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም።
ከዚያም እጆቹን በላያቸው ላይ እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አቀረቧቸው። ደቀ መዛሙርቱ ግን ሕፃናቱን ያመጡትን ሰዎች ገሠጿቸው።
እጁንም ከጫነባቸው በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነሥቶ ሄደ።
“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
እጁንም በላይዋ ጫነ፤ እርሷም ወዲያው ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
ፀሓይ መጥለቂያ ላይም፣ የተለያየ ሕመም ያደረባቸውን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።
እነርሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው አሰናበቷቸው።
እነዚህንም አምጥተው ሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው፤ እነርሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።
ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ።
ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።
በማንም ላይ እጅ ለመጫን አትቸኵል፤ ከሌሎችም ጋራ በኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ።