ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ፣ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ፣ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።
ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።
በግብጽም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።
ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጕልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።
እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።
የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያቆማቸዋል።