ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ።
“እንደዚሁም፣ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬአቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ።
የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።”
ከዚያም የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።
የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጥጦ ዐልቋል፤ ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤ ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣ ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣ በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣ ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል።
በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።
“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።
ኤፍሬም ተመታ፤ ሥራቸው ደረቀ፤ ፍሬም አያፈሩም፤ ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”