“እንደዚሁም፣ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬአቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ።
ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደ ዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ።
ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ።