የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤
እስራኤላውያን ያልሆኑትን ከአሞራውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን የተረፉትን ሕዝቦች ሁሉ፣
እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።
የንስያና የሐጢፋ ዘሮች፤
የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤
የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፣
ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤቴም የተወለዱ ሌሎች ባሪያዎች ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ይልቅ ብዙ የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች ነበሩኝ።