የከተማዪቱም መጠን በሰሜን አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ፣ በደቡብ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ፣ በምሥራቅ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ፣ የምዕራቡም እንዲሁ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ይሆናል።
የከተማዪቱ ከብት ማሰማሪያ ቦታ፣ በሰሜን ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በደቡብ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምሥራቅ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምዕራብም ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ ይሆናል።
ከተማዪቱም ርዝመቷና ስፋቷ እኩል ሆኖ አራት ማእዘን ነበረች። እርሱም ከተማዪቱን በዘንጉ ለካ፤ ርዝመቷም ዐሥራ ሁለት ሺሕ ምዕራፍ ሆነ፤ ስፋቷና ከፍታዋም እንዲሁ ሆነ።