የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና።
ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣
በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያሉት ክፍሎች ስፋት በየደርቡ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ሕንጻ አሠራሩ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ፣ ወደ ላይ በተሄደ ቍጥር የክፍሎቹ ስፋት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመካከለኛው ደርብ በኩል አድርጎ ከታች ወደ ላይ የተዘረጋም ደረጃ አለ።
ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ።
አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው።