ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ።
ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ።
ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋራ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣
ከዚያም ያ ሰው በበሩ አጠገብ ባለው መግቢያ አድርጎ፣ ለሰሜን ትይዩ ወደሆኑት ወደ ካህናቱ የተቀደሱ ክፍሎች አመጣኝ፤ በምዕራቡም መዳረሻ ያለውን ቦታ አሳየኝ።
ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
“በጠባቡ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ እላችኋለሁ፤ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም።