እኔ በማዘጋጅላችሁም መሥዋዕት እስክትጠግቡ ሥብ ትበላላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።
ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣ በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቍጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።
እንደ አውራ በግና እንደ ጠቦት፤ እንደ ፍየልና እንደ ወይፈን፣ የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም መሳፍንት ደም ትጠጣላችሁ፤ እነዚህ ሁሉ የሠቡ የባሳን ከብቶች ናቸው።
በገበታዬም ፈረሶችንና ፈረሰኞችን፣ ኀያላን ሰዎችንና ከየወገኑ የሆኑትን ወታደሮች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።