እንደ አውራ በግና እንደ ጠቦት፤ እንደ ፍየልና እንደ ወይፈን፣ የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም መሳፍንት ደም ትጠጣላችሁ፤ እነዚህ ሁሉ የሠቡ የባሳን ከብቶች ናቸው።
ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።
በሸንበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣ በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኰርማ መንጋ ገሥጽ፤ ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ ጦርነትን የሚወድዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።
የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ ሥብ ጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።
ጐሽ ዐብሯቸው፣ ኰርማም ከወይፈን ጋራ ይወድቃል፤ ምድራቸው በደም ትርሳለች፤ ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።
ነገር ግን ይህ የማየው ምንድን ነው? እጅግ ፈርተዋል፤ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው፤ ብርቱ ጦረኞቻቸው ተሸንፈዋል፤ ዘወር ብለውም ሳያዩ፣ በፍጥነት እየሸሹ ነው፤ በየቦታውም ሽብር አለ፣” ይላል እግዚአብሔር።
“እናንተ ርስቴን የበዘበዛችሁ ሆይ፤ ደስ ስላላችሁና ሐሤትም ስላደረጋችሁ፣ በመስክ እንዳለች ጊደር ስለ ፈነጫችሁ፤ እንደ ድንጉላ ፈረስ ስለ አሽካካችሁ፤
ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ ወደ መታረጃም ይውረዱ! የሚቀጡበት ጊዜ፣ ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው!
“እንደ ጠቦት፣ እንደ አውራ በግና እንደ ፍየል፣ ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።
አንተንና በወንዞችህ ያለውን ዓሣ ሁሉ፣ በምድረ በዳ እጥላለሁ። በገላጣ መሬት ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህ፣ የሚያነሣህም አይኖርም። ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች፣ ምግብ እንድትሆን አሳልፌ እሰጥሃለሁ።
“ ‘መንጋዬ ስለ ሆናችሁት ስለ እናንተ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በበግና በበግ መካከል፣ በአውራ በግና በአውራ ፍየል መካከል እፈርዳለሁ።
በሕያውነቴ እምላለሁ፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እረኞቼ መንጋዬን ስላልፈለጉ፣ ከመንጋዬም ይልቅ ራሳቸውን ስለ ተንከባከቡ፣ መንጋዬ እረኛ ዐጥቶ ለንጥቂያ ተዳርጓል፤ ለአራዊትም ሁሉ መብል ሆኗል።
እኔ በማዘጋጅላችሁም መሥዋዕት እስክትጠግቡ ሥብ ትበላላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።
እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤
የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።
የቀሩት ደግሞ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው በልተው ጠገቡ።