ከዚያም ውሆቿን አጠራለሁ፤ ወንዞቿም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ብዙ ውሃ ባለበት አጠገብ ያለውን፣ የከብት መንጋዋን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የሰው እግር አይረጋግጠውም፤ የከብትም ኰቴ አያደፈርሰውም።
ግብጽን ባድማ ሳደርጋት፣ ምድሪቱም ያላትን ሁሉ ያጣች ስትሆን፣ በዚያም የሚኖሩትን ሁሉ ስመታ፣ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’