ብዙ ውሃ ባለበት አጠገብ ያለውን፣ የከብት መንጋዋን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የሰው እግር አይረጋግጠውም፤ የከብትም ኰቴ አያደፈርሰውም።
የሰው እግርም ሆነ የእንስሳ ኰቴ በውስጧ አያልፍም፤ እስከ አርባ ዓመት ማንም አይኖርባትም።
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤ ሰዎችህንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ።
የአባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤ በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
ከዚያም ውሆቿን አጠራለሁ፤ ወንዞቿም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ “ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣ በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤ በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።
በለምለሙ መስክ ላይ መመገቡ አይበቃችሁምን? የተረፈውን መሰማሪያችሁን ደግሞ በእግራችሁ መረጋገጥ ይገባችኋልን? ንጹሕ ውሃ መጠጣቱ አይበቃችሁምን? የተረፈውንስ በእግራችሁ ማደፍረስ ይገባችኋልን?