በባድማ መሬቶች መካከል፣ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቻቸውም፣ ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
የግብጽን ምድር ከጠፉት ምድሮች መካከል እንደ አንዱ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም በፈራረሱት ከተሞች መካከል አርባ ዓመት ባድማ ይሆናሉ፤ ግብጻውያንንም በአሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።
ግብጽ ባድማና ምድረ በዳ ትሆናለች፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። “ ‘ “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ እኔም ሠርቼዋለሁ” ብለሃልና፤