Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 30:6

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የግብጽ ተባባሪዎች ይወድቃሉ። የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል። ከሚግዶል እስከ አስዋን፣ በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ ረዓብን የሚረዱ እንኳ ይሰግዱለታል።

ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

እነሆ፤ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ አንዳንዶች ከሰሜን ሌሎች ከምዕራብ፣ የቀሩት ደግሞ ከሲኒም ይመጣሉ።”

“እናንተ፣ ‘እኛ ተዋጊዎች ነን፤ በጦርነትም ብርቱ ነን’ ልትሉ እንዴት ቻላችሁ?

ስለዚህ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በወንዞችህ ላይ ተነሥቻለሁ፤ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል እስከ አስዋን ከዚያም እስከ ኢትዮጵያ ወሰን ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ።

ምድሪቱን ጠፍና ባድማ አደርጋታለሁ፤ የምትመካበት ጕልበቷ እንዳልነበረ ይሆናል፤ የእስራኤልም ተራሮች ማንም እንዳያልፍባቸው ባድማ ይሆናሉ።

ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች