ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ ሰይፋቸውን በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣ በአንተ ላይ አመጣለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፤ ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።
የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።
እንደ ክፋቱ መጠን የሥራውን ይከፍለው ዘንድ፣ ለአሕዛብ ገዥ አሳልፌ ሰጠሁት። አውጥቼ ጥዬዋለሁ፤
ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተዉት ሄደዋል።
ከሕዝቦች ሁሉ እጅግ ጨካኝ በሆኑት፣ በኀያላን ሰዎች ሰይፍ፣ ያከማቸኸው ሰራዊት እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ የግብጽን ኵራት ያንኰታኵታሉ፤ የሰራዊቷም ብዛት ይጠፋል፤
ተራሮችህን በሬሳ እሞላለሁ፤ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ በተራሮችህ፣ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ ይወድቃሉ።
አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ ያሉ ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ነጣቂ አሞሮችና የዱር አራዊት ይበሏችሁ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።
ሽማግሌ የማያከብር፣ ለብላቴና የማይራራ፣ ሲያዩት የሚያስፈራ ሕዝብ ነው።