“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣ ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብጽን ሕዝብ እደመስሳለሁ።
እርሱም መጥቶ ግብጽን ይወጋል፤ ሞት የሚገባቸውን ለሞት፣ ለምርኮ የተመደቡትን ወደ ምርኮ፣ ለሰይፍ የተዳረጉትን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።
ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣ በአንተ ላይ አመጣለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፤ ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ግብጽን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጣለሁ፤ ሀብቷን ሁሉ ያግዛል፤ ለሰራዊቱም ደመወዝ ይሆን ዘንድ ምድሪቱን ይበዘብዛል፤ ይመዘብራልም።
እንደ ክፋቱ መጠን የሥራውን ይከፍለው ዘንድ፣ ለአሕዛብ ገዥ አሳልፌ ሰጠሁት። አውጥቼ ጥዬዋለሁ፤
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቍጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፤ “ ‘በክብር ከአንተ ጋራ ማን ሊወዳደር ይችላል?