“ ‘ድዳን ግላስ በማቅረብ ከአንቺ ጋራ ትነግድ ነበር።
የኵሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆች፦ ሳባ፣ ድዳን ናቸው።
ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ፤ የድዳንም ልጆች፦ አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ናቸው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ክንዴን በኤዶም ላይ አነሣለሁ፤ ሰዎቹንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።
“ ‘የድዳን ሰዎች ከአንቺ ጋራ ተገበያዩ፤ ብዙ የጠረፍ አገሮችም የንግድ ደንበኞችሽ ነበሩ፤ በዝኆን ጥርስና በዞጲ ሸቀጥሽን ይገዙ ነበር።
ዌንዳንና ያዋን ከኦሴል መጥተው ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር፤ ቀልጦ የተሠራ ብረትን፣ ብርጕድንና ከሙንን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
ሳባና ድዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና መንደሮቿም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፤ “ልትዘርፍ መጣህን? ሰራዊትህን ያሰባሰብኸው ለመበዝበዝ፣ ወርቅና ብሩን አጋብሶ ለመሄድ፣ ከብቱንና ሸቀጡን ለመውሰድ፣ ብዙ ምርኮ ይዞ ለመመለስ ነውን?” ’